በኢትዮጵያ 5 ሚሊየን ዜጎች የመስማት ችግር አለባቸው ተባለ።

የአለም የጤና ድርጅት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ 5 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጎች የመስማት ችግር እንዳለባቸው ጠቁሟል፡፡

ድርጅቱ ይህንን ያለው በዛሬው እለት በተከበረው የአለም የመስማት ቀን ላይ ነው፡፡

በዛሬው እለት በመላው አለም የመስማት ቀን እየተከበረ ይገኛል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ ቀኑ የመስማት ህክምና ለሁሉም በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኝው፡፡

የመስማት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ15ኛ ጊዜ ሲከበረ በኢትዮጵያ ደግሞ ለአራተኛ ጊዜ ነው የተከበረው፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ 5 ነጥብ 5 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ የመስማት ችግር እንዳለባቸው ነው የአለም የጤና ድርጅት መረጃ የሚያሳየው፡፡

በሀገራችን ደግሞ ከዚሁ ከመስማት ችግር ጋር በተያያዘ ወደ 5 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች የመስማት ችግር እንዳለባቸው ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

እንደዚሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ከአምስት ሰው አንዱ የመስማት ችግር እንዳለበት ነው የተጠቆመው፡፡

የቅዱስ ፓውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ እና ከሲቢኤም ድርጅት ጋር በተያያዘ የአለም የመስማት ቀን በዛሬው እለት አክብረወል፡፡

ሰዎች በተፈጥሮ የተሰጣቸውን የመስማት ክህሎት አንድ ጊዜ የሚያጡ ከሆነ ወደ መጀመሪያው መመለስ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅሰው ሰዎች በየጊዜው የጆሮዋቸውን ጤንነት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

በ2019 የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም ዙሪያ 466 ሚሊየን ሰዎች የመስማት ችግር እንዳለባቸውም አስታውቆ ነበር፡፡

ድርጅቱ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2050 የመስማት ችግር ያለባቸው ሰዎች አሁን ከተገለጸው ቁጥር በእጥፍ ሊጨምር እንደሚችልም ተንብየዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *