በሶማሊያ የመጀመሪያዋ ሴት አሽከርካሪ፡፡

የሴቶች መብት በእጅጉ ከተገደቡባቸዉ ሀገራት መካከል አንዷ ሶማሊያ ናት፡፡

በዚች ሃገር ሴቶች መኪና ማሽከርከር እንኳ አይፈቀድላቸዉም፡፡

አሁን አሁን ግን ሴቶች መኪና ማሽከርከርን ጨምሮ ለወንዶች ብቻ የተሰጡ የሚመስሉ ስራዎች ላይ ለመሳተፍ ድምጻቸዉን እያሰሙ ይገኛሉ፡፡

አልጃዚራ በሶማሊያ የመጀመሪያዋን ሴት አሽከርካሪ ዘገባ ይዞ ወቷል ሳይናብ አብዲካሪን ትባላለች፡፡

በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ጎዳና ላይ ባጃጅ ማሽከርከር መቻሏ በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት አሽከርካሪ አስብሏታል።

በሶማሊያ አሁንም ድረስ የመካኒክነትና የማሽከርከር የሙያ ዘርፎችን ጨምሮ ሌሎችም ስራዎች ለወንዶች የተተው እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ለዚሁ ደግሞ በሀጋሪቱ ለዘመናት የቆየው የወግ አጥባቂነት ባህል ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ነው የሚነገረው።

ነገር ግን የ28 አመቷ ሳይናብ ይህንን ባህል ወደ ጎን በመተው ለ11 ወራት ያህል ባጃጅ በመጠገንና በማሽከርከር ስራ ላይ ተሰማርታ እንደቆየች ገልፃለች።

“ሳሽከረክር የሚያዩኝ ወንዶች ይንቁኛል፣ ለኔ ግን ስራ እስከሆነ ድረስ እሰራለሁ እገኛለሁ፤ ሰርቼ የምመግበዉ የራሴ ወንድ ልጅ ሳይቀር በስራዬ ደስተኛ አይደለም” ስትል ያለዉን ጫና አስረድታለች፡፡

በጅብሪል ሙሃመድ
የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *