የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው፣ በጥቃቱ በትንሹ 30 የሚሆኑ ሰዎች ሲገደሉ ከ170 በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡
በየመን ዋና ከተማ ሰነኣ የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከሚገኙት ስደተኞች መካከል፣ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ እንደዳልቀሩ ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡
አደጋው የደረሰው በየመን የሚገኘው የሀውቲ አማጽያን በሳውዲ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቡ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ሳውዲ በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ እንደሆነም ኤጀንሲው አስታዉቋል፡፡
በሄኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም











