ኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት፣የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ በህዳሴው ድርድር ላይ ይግቡ የሚለውን ሀሳብ እንደማትቀበለው አስታወቀች፡፡

ግብፅ እና ሱዳን የድርድር ሂደቱ በተባበሩት መንግሰስታት ድርጅት፣በአውሮፓ ህብረት እና በአሜሪካ አማካኝነት እንዲካሄድ ቢፈልጉም፣ ኢትዮጵያ ግን ለአፍሪካ ባላት አክብሮት ድርድሩ መቀጠል ያለበት በአፍሪካ ህብረት ነው ብላ እንደምታምን ገልጻለች፡፡

የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳስታወቁት፣ ፣የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ዲሞክራቲክ ኮንጎ አደራዳሪ ልዑካን አዲስ አበባ መጥተው ውይይት ተደርጓል ብለዋል።

የልዑካን ቡድኑ ግብፅና ሱዳን በድርድሩ ላይ አሜሪካ ፣የአውሮፓ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጣልቃ እንዲገቡ ፍላጎት እንዳላቸው ቢያሳውቅም፣ ኢትዮጵያ ግን ሀሳቡን እንደማትቀበለው አስታውቃለች ነው ያሉት አምባሳደሩ።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ችግር በአፍሪካውን መፈታት እንዳለበት ታምናለች ያሉት ቃልአቀባዩ ፣ይህንን ደግሞ የወቅቱ ሊቀመንበር የሆነችው ዲሞክራቲክ ኮንጎም ማመን አለባት ብለዋል።

ግብፅና ሱዳን አቋማቸውን በመለዋወጥ የተለያዩ አደራዳሪዎች እንዲመጡ ቢፈልጉም በኢትዮጵያ በኩል ግን ተቀባይነት እንደሌለው የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታዉቋል፡፡

በአባቱ መረቀ
የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *