በአሜሪካ የኮቪድ -19 ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን መጠየቅ ይችላሉ ተባለ፡፡

የመጨረሻውን ክትባት ከተከተቡ ሁለት ሳምንት የሆናቸው ከቫይረሱ ስጋት ነጻ መሆናቸውን የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ ) አሳውቋል፡፡

ማዕከሉ እንዳለው ክትባቱን በአግባቡ የወሰዱ ሰዎች ያለ ማስክ በቤት ውስጥ መንቀሳቀስ ይችላሉ ሲል መመሪያ አውጥቷል ፡፡

አሜሪካ እስካሁን ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿን መከተቧን አሳውቃለች፤ ይህ አዲስ የደህንነት መመሪያ ይፋ የተደረገው ትላንት የኮሮና ቫይረስ ግብረ- ኃይል በዋይት ሃውስ በሰጠው መግለጫ ላይ ነው።

በወጣው መመሪያ መሰረትም የኮሮና ቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ማድረግ ይችላሉ ከተባሉት ውስጥ

  • ከተከተቡ ሰዎች ጋር ያለ ጭምብልም ሆነ አካላዊ ርቀታቸውን ሳይጠብቁ በቤት ውስጥ መገናኘት ይችላሉ፡፡
  • በአንድ ቤት ውስጥ ከሚኖሩና ተጋላጭ የጤና እክል እና ህመም የሌላቸው የማህበረሰቡ አካላት ካልሆኑ ካልተከተቡ የቤተሰብ አባላት ጋር በቤት ውስጥ መገናኘት ጨምሮ እኚህ ሰዎች በኮቪድ-19 ቢጋለጡም ምርመራዎችን አያደርጉም እንዲሁም ለይቶ ማቆያ ውስጥ አይገቡም፤ ምልክት እስካላሳዩ ነው የተባለው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *