በኢትዮጵያ ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ የኮቪድ 19 ክትባት መስጠት ይጀመራል ተብሏል፡፡

የጤና ሚኒስቴር እንዳለዉ መጪው ቅዳሜ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም በሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ክትባቱ እንደሚሰጥ ታዉቋል፡፡

ክትባቱን ለመስጠት የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች ማከናወኑንም ሚንስቴሩ ገልጿል፡፡

በመጀመሪያም ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ማለትም የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች፣ እድሜያቸው ከፍ ያሉ እና ተጓዳኝ ህመም ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱን እንደሚያገኙ ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያ በኮቫክስ ዓለም አቀፍ ጥምረት አማካኝነት 2 .2 ሚሊዮን የመጀመሪያው ዙር የኮቪድ 19 ክትባት ማግኘቷ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *