የአማራ ክልል ምክር ቤት 17 መደበኛ ጉባኤዉን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባኤዉ ለሶስት ቀናት በባህርዳር ከተማ የሚካሄድ ሲሆን የተቋማትን የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ይገመግማል ተብሏል።

የዋና ኦዲተርና የጠቅላይ ፍርድ ቤት የግማሽ ዓመት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበትም ተገልጿል።

በጉባኤው የአብክመ የቴምብር ቀረጥ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣ የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል፣ የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅም በውይይት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ልዩ ልዩ ሹመቶችን ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 02 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *