የታንዛኒያ ባለስልጣናት ጆን ማጉፋሊ በኮሮና አልተያዘም አሉ፡፡

የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፋሊ ከሰሞኑ በኮሮና ተይዘዋል ሲባል ነበር የተነገረው፡፡

አሁን ላይ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ፕሬዝዳንቱ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው ኮሮናም አልያዛቸውም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ካሲም ማጂሊዋ ፕሬዝዳንታችን በስራ ገበታ ላይ ናቸው በኮሮና ተይዘዋል ብለው የሚያወሩት ምራባዊያን ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ማጉፋሊ የኮሮና ቫይረስ በእንፋሎት አጥፍተናዋል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ አፍሪካዊው ዶናልድ ትራምፕ እስከ መባል ደርሰው ነበር፡፡

ሄኖክ ወልደገብርኤል
መጋቢት 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *