የአሜሪካና የሰሜን ኮርያ ውጥረት መቋጫ አላገኘም፡፡

አሜሪካ ከሰሜን ኮርያ ጋር ለመመካከር ተደጋጋሚ ጥረት ብታደርግም በሰሜን ኮሪያ በኩል ግን ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

አዲሱ የባይደን አስተዳደር ከየካቲት ወር ጀምሮ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ውይይት ለማድረግ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ አሁንም በሰሜን ኮሪያ በኩል ምንም አይነት ምላሽ አለማግኘቱን መረጃው ጠቅሷል።

አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ እያካሄደች የምትገኘውን የኒዉክሌር ማበልፀግና የሚሳኤል ፕሮግራሟን አቁሚ በሚል ውዝግብ ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል።

ሰሜን ኮሪያም የኒዉክሌያር ፕሮግራሟን አላቆምም በማለቷ በአሜሪካ የኢኮኖሚ ማእቀብ ተጥሎባታል፡፡

ከዚህ ቀደም ሁለቱም ሀገራት 3 ጊዜ ተገናኝተው ምክክር ያደረጉ ሲሆን ሁሉም ያለስምምነት ተጠናቀዋል፡፡

አሜሪካ ብቻም ሳትሆን የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ሰሜን ኮሪያ ኒዉክሌር ከማበልፀግ እንድታቆም ግፊት ቢያደርጉም አሁንም ደረስ የመጣ ለውጥ አለመኖሩ ነዉ የሚነገረዉ፡፡

ሰሜን ኮሪያ የኒዉክሌር ፕሮግራሟን ስታቋርት በምትኩ ደግሞ የተጣለባት ማእቀብ እንዲነሳላት ሃሳብ ቢቀርብላትም ፍቃደኛ አለመሆኗን መረጃው አስታውቋል።

አሁን ሰሜን ኮሪያ ለሌላ የምክክር መድረክ ብትጠየቅም አዎንታዊም ይሁን አሉታዊ ምላሽ ሳትሰጥ ከወር በላይ መቆየቷን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *