የአውሮፓ ህብረት አስትራዜኔካ ክትባት ውጤታማና አስተማማኝ ነው አለ፡፡

የአውሮፓ ህብረት የህክምና ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ባደረገው ግምገማ አስትራዜኔካ ለኮቪድ 19 ክትባት አስተማማኝና ውጤታማ ነው ብሏል፡፡

ኤጀንሲው ክትባቱን የመረመረው 13 የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ክትባቱ ከደም መርጋት ጋር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል በሚል በሀገራቸው ጥቅም ላይ እንዳይውል ማገዳቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ኤጀንሲው ክትባቱ ምንም ከደም መርጋት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ያለ ሲሆን ጣልያን፣ስፔን እና ጀርመን ክትባቱ በድጋሚ አገልግሎት ላይ እንዲውል እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ክትባቱን መጠቀም ስለ ሚጀምርበት ቀንም የመወሰን ስልጣኑ የራሱ ነው፡፡

ስዊድን ለመወሰን ጥቂት ቀናት ያስፈልገኛል እያለች ነዉ የአለም ጤና ድርጅት ሀገራት ክትባቱን እንዲጠቀሙ በድጋሚ ጥሪዉን አቅርቧል፡፡
ሮይተርስ

በሄኖክ አስራት
መጋቢት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *