የአውሮፓ ህብረት በማይናማር ወታደራዊ ሀይሎች ላይ ማእቀብ ሊጥል ነው፡፡

ህብረቱ 11 በሚጠጉ የማይናማር ወታደራዊ ሀይሎች ላይ ማእቀብ እንደሚጥል አስታውቋል፡፡

በማይናማር መፈንቅለ መንግስት ላይ የተሳተፉ እና ያቀነባበሩ ከፍተኛ የወታደራዊ ሀይሎች በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ እና የመሳርያ ማእቀብ ሊጣልባቸው እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዳስታወቀው የፊታችን ሰኞ በሰዎቹ ላይ የተጣለው ማእቀብ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል፡፡

ህብረቱ እንዳስታወቀው የመንግስታቱ ድርጅት የማይናማር ሀይሎች የሚያገኙት ፋይናስ እና የጦር መሳርያ ማቋረጥ አለበት ሲልም አስታውቋል፡፡

የህብረቱ 27 አባል ሀገራት ከዚህ በፊት ለማይናማር ያደርጉት የነበረውን ድጋፍ ማቋረጣቸው ይታወሳል፡፡

በማይናማር የሰብአዊ መብት ተከራካሪ እና በመንግስታቱ ድርጅት የማይናማር ተጠሪ ቶም አንድሪው እንደተናገረው በማይናማር ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ጭቆና እና ስቃይ ሊቆም የሚችለው በወታደራዊ ሀይሉ ላይ ማእቀብ ሲጣል ብቻ ነው ብሏል ።

ቢቢሲ

በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *