የኮንትሮባንድ ልብሱ በ34 ኩንታል ቡና በማስመሠል ነው ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል በቱሉ ዲምቱ መቆጣጠርያ ጣብያ የተያዘው፡፡
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የቱሉ ዲምቱ መቆጣጠርያ ጣብያ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መረጃ፣ በትናንትናዉ እለት በኮንትሮባንድ ቁጥጥር ክትትል ዲቪዢን በፌደራል ፖሊስ እና በጉሙሩክ ፈታሾች በጋራ በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ ነዉ ሊያዝ የቻለዉ ብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የጉሙሩክ መቆጣጠርያ ጣቢያዎች የስራ ሂደት ኃላፊ አቶ ዋርዮ ጉዮ እንደነገሩን፣ ድርጊቱ የተፈፀመው ህጋዊ የቡና ማዘዋወርያ ሰነድ በያዘ የጭነት ተሽከርካሪ ነዉ።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም
