በትግራይ ከ 30 ሺህ በላይ እስረኞች ያለአግባብ ከእስር ተለቀዋል—ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለተነሱላቸዉ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ኦነግን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ጥያቄ ከኦነግ የሸፈቱ ኦነግ ሸኔዎች የኢትዮጵያ ጠላት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኦነግ ላለፉት 20 አመታት የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግለት የነበረው በማነው የመሳሪያ ድጋፍስ የሚያደርግለት አካልስ ማን እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ሃይል በጋራ ነዉ መከላከል የሚያስፈልገዉ ብለዋል፡፡

ሀገር ለማፍረስ ከተነሱት የህወሃት ቡድን ጋር ተደራጅተው ኢትዮጵያን ጎድተዋታል ብለዋል፡፡

በትግራይ የህግ ማስከበር እርምጃ ወቅት 200 የሚደርሱ የኦነግ ሸኔ አባላት ሲሰለጥኑ ተገኝተዋልም ብለዋል፡፡

በትግራይ ክልል 30 ሺ የሚደርሱ እስረኞችም ያለአግባብ መፈታታቸዉን አንስተዋል፡፡

30 ሺ የሚጠጉ እስረኞች ያለአግባብ የተፈቱትም የኢትዮጵያን ህዝብ ለመጉዳት በማሰብ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *