ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የጥምር መንግስት ለመመስረት የሚስቻላቸዉን ድምጽ አሁንም ላያገኙ ይችላል ተብሏል፡፡

በእስራኤል ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የጥምር መንግስት ለመመስራት የሚስችላቸዉን ድምጽ ላያገኙ እንደሚችል እየተነገረ ነዉ፡፡

አስራኤል በሁለት አመት ዉስጥ ለ4ኛ ጊዜ በትናትናዉ ዕለት ምርጫ ያካሄደች ቢሆንም እስካሁን ባለዉ የምርጫ ዉጤት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥምር መንግስት መመስረት የሚያስችላቸዉን ድምፅ እንዳላገኙ ነዉ የተነገረዉ፡፡

እስካሁን የቆጠራ ሂደቱ 90 በመቶ መጠናቀቁን ያስታወቀዉ ዘገባዉ፣ በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከቀኝ ዘመም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ ፉክክር ገጥሟቸዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

ኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲን ወክለዉ በተከታታይ ላለፉት 12 ዓመታት እስራኤልን እየመሩ የሚገኙ መሪ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ፈጽመዋል በተባለዉ የሙስና ቅሌት ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ጫናን ላለፉት 2 ዓመታት ሲስተናግዱ መቆየታቸዉ ይታወሳል፡፡

በዚህም አገሪቱ ሶስት ምርጫዎችን ብታደርግም ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ግን አንደኛዉንም ማሸነፍ አልቻሉም፡፡

በትናትናዉ እለትም በ2 ዓመት ዉስጥ 4ኛዉን አገራዊ ምርጫ እስራኤል ያካሄደች ሲሆን ምናልባትም ኔታንያሁ አሁንም የጥምር መንግስት መመስረት የሚያስችላቸዉን ድምጽ ላያገኙ ይችላሉ መባሉን ተከትሎ ከፍተኛ ዉጥረት ዉስጥ እንደሚገኙ መረጃዎች እየጠቆሙ ነዉ፡፡
ቢቢሲ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *