ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ውዝግብ ለመፍታት ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የቀረበላትን የድርድር ሃሳብ ተቀበለች፡፡

ሱዳን ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንባቸው አካባቢዎች፤ የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎችን በማንሳት ከኢትዮጵያ ጋር የክርክር አጀንዳዎችን መክፈቷ የሚታወስ ነው፡፡

ሱዳን በድንበር ጉዳዮች ብቻም ሳይሆን ከህዳሴው ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘም ከኢትዮጵያ ጋር በአዲስ መልክ ውዝግብ መጀመሯም እንዲሁ ይታወቃል፡፡

ይህ ሲሆን በዋናነት አሜሪካና የአፍሪካ ህብረት፤ ጎረቤት ሀገራቱን ለማስማማት ለድርድር በርካታ ጊዚይት ቢቀመጡም በግልጽ የመጣ ለውጥ አለመኖሩ ነው የሚነገረው፡፡

ከሰሞኑ ደግሞ ለሌላ ድርድር በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ላቀረቡት ጥያቄ ሱዳን ፈቃደኛ መሆኗን አስታውቃለች፡፡

በድርድሩ ኢትዮጵያና ሱዳን አሁን ለሚገኙበት ከድንበርና ከህዳሴው ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለማምጣት ምክክር ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቢቢሲ አፍሪካ

በጅብሪል ሙሓመድ
መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *