የሆቴልና ቱሪዝም ስራዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የማደግ እቅድ እንዳለዉ ገለጸ፡፡

ከተመሰረተ 52 ዓመታትን ያስቆጠረዉ የሆቴልና ቱሪዝም ስራዎች ማሰልጠኛ ተቋም አሁን ያለበት ደረጃ ያለዉን ታሪክና ስም የሚመጥን እንዳልሆነ ይነገራል፡፡

ይባስ ብሎም በ2000 ዓ.ም ከኢንስትቲዩት ወደ ማዕከልነት እንዲወርድ ተደርጓል፡፡

የማዕከሉ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ገዛከኝ አባተ እንደነገሩን፣ በዘርፉ የልህቀት ማዕከል(Center of excellence) እንዲሆን በማሰብ በጊዜው የነበሩ አመራሮች ጥያቄ አቅርበዉ ነበር፡፡

ተቋሙ ከሚሰራው ስራ አንጻርና ካለው ዕድሜ ማዕከል የሚለው ስለማይመጥነው ነው ማሻሻያ ወይም Reform እንደሚያስፈልገዉም የማዕከሉ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ገዛከኝ አባተ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ህግ ማዕከል ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በታች መሆኑን ያስታወሱት አቶ ገዛክኝ፣ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ቀዳሚ ተመራጭ የሆነው ተቋሙ ከማዕከል ከፍ ሊል ይገባል በሚል ስራዎች መጀመራቸዉን ነግረዉናል፡፡

ለሀገሪቱ እድገት ወሳኝ መሆኑ የሚነገርለት የቱሪዝም ዘርፉን ለማገዝ ማዕከሉ  በርካታ ተማሪዎችን በሆቴልና ቱሪዝም ሙያ እያሰለጠነ እያስመረቀ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

ማሻሻያው ሲደረግ  ከውጪ የምናስመጣቸውን ባለሙያዎች ቀንሰን እዚሁ በተቋማችን በዲግሪና ከዛም በላይ ብቁ ባለሙያዎችን እንድናሰለጥን ያስችለናል ብለዋል ምክትል ዳይሬክተሩ፡፡

የማዕከሉን ማሻሻያ ሀሳብም ለሚመለከተው አካል በቅርቡ ለማቅረብ ዝግጅት እንዳለ ያነሱት አቶ ገዛሃኝ ዘርፉ ለሀገሪቱ እድገት ካለዉ አስተዋጽኦ አንጻር አዎንታዊ ምላሽ እንደሚያገኝ ያላቸዉን እምነት ገልጸዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

በመቅደላዊት ደረጀ

መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *