‹‹ መርከባችን አትሰምጥም ›› በሚል መሪ ቃል መጋቢት 19 ቀን 2013 ዓ/ም ሊካሄድ የታቀደው ህዝባዊ ሰልፍ ተራዘመ፡፡

በኢትዮጲያ የውስጥ ጉዳይ ላይ በመግባት የእጅ መጠምዘዝ ስራ ለመስራት በሚሞክሩ ተቋማት እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ እንዲስተጓጎል በሚሰሩ አካላት ላይ ተቃውሞ ለማሰማት መጋቢት 19 ቀን 2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሊካሄድ የታቀደው ሰላማዊ ሰልፍ መሰረዙን የሰላማዊ ሰልፉ ኮሚቴ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዮናስ ቬጋስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቀዋል፡፡

በእለቱ የከተማ አስተዳደሩ የተያዘ ፕሮግራም መኖሩን በማሳወቁ ምክንያት ሰላማዊ ሰልፉን ማካሄድ ያለመቻሉን አቶ ዮናስ ነግረውናል፡፡

አቶ ዮናስ እንደነገሩን የዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ዋና ዓላማ ስለ ኢትዮጵያ ትክክለኛ መረጃ ለዓለም እንዳይደርስ በሚሰሩ ሀገራት እና አለምአቀፍ ሚዲያዎች ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ህዝባዊ ሰልፍን ማካሄድ አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡

ይሁን እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩል በእለቱ በከተማዋ ተያዘ በተባለው ሌላ ፕሮግራም ምክንያት የፊታችን መጋቢት 19 በመስቀል አደባባይ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ሊካሄድ የነበረው ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ሊራዘም መቻሉን ነግረውናል፡፡

በመሆኑም ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ በቀጣይ የማካሄድ እቅዱ እንዳለና ሰላማዊ ሰልፍ የሚካሄድበትንም ትክክለኛ ቀን ለህዝቡ በድጋሚ ይፋ እንደሚደረግ የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየዉልሰዉ ገዝሙ
መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *