በምያንማር አመጽ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ 320 ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል ተባለ፡፡

ጉዳዮን እየተከታተሉ የሚገኙ አካላት እንዳሉት በምያንማር ህዝባዊ አድማው ከተቀሰቀሰ አንስቶ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎችና በተቃውሞ አድራጊዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ነዉ 320 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸው የተገለጸዉ፡፡

የህጻናት አድን ድርጅት በበኩሉ ከሟቾች መካከል አንዲት የ7 አመት ህጻንን ጨምሮ በአመጹ ከ20 በላይ ህጻናት ህይወታቸው ማለፉን አመላክቷል፡፡

እንዲሁም ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ወንዶች ሲሆኑ በአብዛኛው ወጣቶች እንደሆኑም ተነግሯል፡፡

በሀገሪቱ በየቀኑ አሁንም ድረስ ንጹሃን ዜጎች እየተገደሉ እንደሚገኙም ድርጅቱ ገልጿል፡፡

በዚህም የሟቾች ቁጥር አሁን ከተጠቀሰው አሃዝ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ነዉ ያስታወቀዉ፡፡

አመጹን ለማስቆም አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሀገራት በሃገሪቷ ላይ ማእቀብ ቢጥሉም አሁንም ድረስ በምያንማር መረጋጋት እንደማይታይ መረጃዉ ጠቁሟል፡፡

ሮይተርስ

በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *