ቻይና በአምስት የእንግሊዝ የፓርላማ አባላት ላይ ማዕቀብ ጣለች፡፡

የፓርላማ አባላቱ ማዕቀብ የተጣለባቸዉም በሃሰተኛ መረጃዎች የቻይናን ስም እያጠፉ ነዉ በሚል ነዉ፡፡

ቻይና በዊጋር ሙስሊም ማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸመች ነዉ በሚል ምዕራባዊያን ይወነጅሏታል፡፡

በዚህም የአዉሮፓ ህብረትን ጨምሮ እንግሊዝ፣አሜሪካና ካናዳ በቻይና ላይ ማዕቀብ መጣላቸዉን ተከትሎ ነዉ ቻይና በእንግሊዝ የፓርላማ አባላት ላይ ማዕቀብ መጣሏ የተሰማዉ፡፡

ቻይና ከፓርላማ አባላቱ በተጨማሪም ስሜን እያጠፉ ነዉ ያለቻቸዉ ሶስት እንግሊዛዊያን ታዋቂ ግለሰቦች ላይም ማዕቀብ መጣሏ ታዉቋል፡፡

ይህም በእንግሊዝና በቻይና መካከል ያለዉን ዉጥረት እንዳያባብሰዉ ተሰግቷል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በሆንግኮንግ ጉዳይ ከፍተኛ ዉዝግብ ዉስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

አልጀዚራ

በሙሉቀን አሰፋ
መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *