የፓርቲዎች የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል ተዘጋጀ ።

ይህንን ድልድል የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በዛሬው እለት በሒልተን ሆቴል በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ አስታውቋል ።

በስድስተኛ ሃገራዊ ምርጫ ላይ ለሚወዳደሩት 46 የፓለቲካ ፓርቲዎች የተመደበው የአየር ሰዓት አምድም እንደሚከተለው ቀርቧል።

የመንግስት ራዲዮ ጣቢያዎች ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር ቀን እና ማታ ሁለት ጊዜ ለሰላሳ ደቂቃ ያክል ክርክሩን እንዲያካሂድ የተመደበ ሲሆን

የመንግስት የህዝብ ቴሌቪዥኖች ከሰኞ እስከ ዓርብ ዘወትር ቀንና ማታ ለሰላሳ ደቂቃ

ሌሎች የክልል ሚዲያዎች ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር ማታ ማታ ለሰላሳ ደቂቃ

የንግድ የራዲዮ ተቋማት ከሰኞ እስከ አርብ ለሰላሳ ደቂቃ ጠዋት ጠዋት ብቻ

የንግድ የቴለቪዥን ጣቢያዎች በሳምንት ሁለት ቀን ዘወትር ማታ ማታ ሰላሳ ደቂቃ

ጋዜጣን በተመለከተ አዲስ ዘመን ላይ በ ሳምንት ሶስት ቀን ሽፋን እንዲሰጥበት በብሮድካስት ባለስልጣን ሀሳብ ቀርቧል።

በዚህ የሰዓት ድልድል ላይ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች እንደሚካተቱበት የተነገረ ሲሆን ባለስልጣናኑ ከምርጫ ቦርድ ጋር በመነጋገር የእጩዎችን የአየር ሰዓት ድልድል እንደሚያሳዉቅ አስታውቋል ።

በድልድሉ ላይ ከየሚዲያ ተቋማት የተለያዩ ጥያቄች የቀረቡ ሲሆን በባለስልጣኑ ምላሽ ተሰቶባቸዋል ።

በዛሬም እለትም የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመገናኛ ብዙሃን በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ ምደባ፣ በምርጫ ዘገባዎች ፣ በመራጮች ትምህርትና ለምርጫው ስኬታማነት ያላቸውን ሚና መጫወት በሚችሉበት አግባብ ላይ ለጋዜጠኞች እና ለሚዲያ ሃላፊዎች ስልጠና ተስቷል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየዉልሰዉ ገዝሙ
መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *