ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር ገለጸ፡፡

ሚንስቴሩ እንዳለዉ በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስምንት ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም ይገኛል ተብሎ ከታሰበው 2 ነጥብ 55 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን አስታዉቋል፡፡

የወጪ ንግድ አፈጻጸሙ ከዕቅዱ አንፃር የ82 በመቶ በማሳካት ከ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 1 ነጥብ 81 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነጻጸር የ16በመቶ ወይም የ290 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ብልጫ ገቢ መመዝገቡን ከሚንስቴሩ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *