በታይዋን ባቡሩ በዋሻ ውስጥ ሲያልፍ ከሀዲድ በመውጣቱ ምክንያት 34 ሰዎች ሞቱ፡፡

በታይዋን 350 ሰዎች ጭኖ የነበረ ባቡር በዋሻ ውስጥ ሲያልፍ ከሀዲድ በመውጣቱ ምክንያት ቢያንስ 34 ሰዎች ሲሞቱ 70 የሚሆኑት ደግሞ መውጣት እንዳልቻሉ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የተጎዱ ተሳፋሪዎች በርካቶች ሲሆኑ ፤ ለማዳን በሚጥሩበት ወቅት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ነፍስ አድን ሰራተኞችም ጥቂት እንዳልሆኑ ተዘግቧል፡፡

ባቡሩ ከመዲናዋ ታይፔይ ወደ ታይቱንግ አመታዊ ፌስቲቫል ለማክበር የሚጓዙ ሰዎች ነበር ያሳፈረው፡፡

የተሳፈረው ሰው በርካታ ስለነበር ብዙ ተሳፋሪ ቆሞ ነበር ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሄኖክ አስራት
መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *