በናይጄሪያ የመንግስት ሆስፒታል ዶክተሮች አድማ መቱ፡፡

ክፍያ አነሰን፣ ስራውን ለመከወን የሚሆን በቂ የግብዓት አቅርቦት የለም፣ ከኮቪድም ሆነ ከሌሎች ጤናና ደህንነት ላይ አደጋ ከሚጋርጡ ሁኔታዎች መከላከያ ቁሳቁሶችና መሳርያዎች እጥረት አለ በሚል ነው ዶክተሮቹ ላልተወሰነ ጊዜ አድማ መቱ የተባለዉ፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጊዜ የአደጋ ጊዜ አበልም ያስፈልገናል ብለዋል ዶክተሮቹ፡፡

አድማው የተጠራው በብሔራዊ የዶክረቶች ማህበር (Nard) ሲሆን ይህ ማህበር የሀገሪቱን ዶክተሮች 40 በመቶ ያቀፈ መሆኑ ይነገራል፡፡

በርካታ ሆስፒታሎች እንደ አልጋና መድሀኒት ያሉ መሰረታዊ የሆስፒታል ፍላጎቶች እንደሚጎላቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

መንግስት እንደዚህ ያሉ አድማዎች ከወረርሽኙ ጋር እያደረግን ያለውን ትግል ይበልጥ አስቸጋሪ ያደርግብናል ብሏል፡፡

በተለይም 40 ሚሊዮን የአስትራዜኒካ ክትባቱን በማድረስ ረገድ መሰናክል ይሆናል ብሏል፡፡

እንደ ማህበሩ ገለፃ 17 ዶክተሮች በኮቪድ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

የአደጋ ጊዜ አበሉ ኮቪድ ከገባ ጀምሮ ለሶስት ወር ከተሰጠ በኋላ እንደቆመ ማህበሩ ገልጿል፡

በናይጄሪያ 160 ሺህ ሰው በኮቪድ 19 ሲጠቃ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ህይወታቸዉ ማለፉ ተገልጿል፡፡

ቢቢሲ

በሔኖክ አስራት
መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *