የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተበረከተለት፡፡

ሽልማቱን የሰጠዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነዉ፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ለ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ላሳካው ዉጤት ነዉ ከአዲስ ከአበባ ከተማ አስተዳደር የ5.6 ሚሊዮን ብር ሽልማት የተበረከተለት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ላስመዘገበው ውጤት እጅግ የላቀ ክብርና አድናቆት እንዳለው ም/ከንቲባ አዳነች አበቤ ገልጸዋል።

በእግር ኳስ በግል የሚመዘገብ ውጤት የለም ያሉት ም/ከንቲባዋ፤ ውጤት የሚመጣው ሜዳ ላይ በሚጫወቱት ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆን፣ አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ ተጠባባቂዎች፣ ወጌሻዎች፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ አማካሪዎና ደጋፊዎች በአንድነት ሲሰሩ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በዚህም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ደስታ የተሰማዉ መሆኑንና ያለዉን አጋርነትም ለማረጋገጥ የ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ሽልማት ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *