የዓለም ንግድ ድርጅት የኮቪድ-19 ክትባት ከመጣ ወዲህ መሻሻል ማሳየቱ ተነገረ፡፡

ድርጅቱ እንዳለዉ በፈረንጆቹ በ2021 የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝ ተቋቁሞ የ8 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን አስታውቋል፡፡

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በዓለም የንግድና ሌሎችም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ተቀዛቅሰው የነበሩ በመሆናቸው ድርጅቱ በ2020 እድገቱ በ5.3 በመቶ ቀንሶ እንደነበር ገልጿል፡፡

የኮቪድ 19 ክትባት ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ፣ በሀገራት መካከል የሚደረገው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንደገና ማንሰራራት በማሳየቱ ፤ በጥቅምት ወር ድርጅቱ በ7 ነጥብ 2 በመቶ ያድጋል ተብሎ ከተጠበቀው በላይ በ0 ነጥብ 8 ብልጫ ማሳየቱንም ነው የገለጸው፡፡

የአለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢውያላ እንደሚሉት፤ በንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ለመጣው መሻሻል የኮሮና ቫይረስ ክትባት ትልቅ አስተዋጸኦ እንደነበረው ገልጸዋል፡፡

ሃላፊዋ አክለውም ምንም እንኳን የንግድ እንቅስቃሴዎች መሻሻል ቢሳዩም አሁንም ድረስ የኮቪድ 19 ተጽዕኖ ከባድ ሆኖ መቀጠሉን አንስተዋል፡፡

ስለሆንም እድገቱን አስጠብቆ ለመቆየት ክትባቶችን በመከተብና የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመተግበር በሀገራት መካከል የሚደረገውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ማከናወን ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቢቢሲ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *