የሚያዚያ ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዳለዉ፣ ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ብሏል።

በሚያዚያ ወር የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በሊትር 43 ብር ከ70 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡

ይህም በመጋቢት ወር ሲሸጥበት ከነበረበት ዋጋ የ5 ብር ከ5 ሳንቲም ጭማሪ እንዳለው ያሳያል።

የንግድ ሚንስቴር እንዳለዉ በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደርግ ይችላል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *