በእነ ጃዋር መሀመድ ላይ በዝግ ችሎት ምስክር ላሰማ ሲል ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ጥያቄ ፍርድ ቤት ዉድቅ አደረገ፡፡

ዐቃቤ ህግ ባለፈው ቀጠሮው ለምስክሮቼ ደህንነት ሲባል ከመጋረጃ በስተ ጀርባ እና በዝግ ችሎት ምስክሮቼን ላሰማ ሲል አቤቱታ አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ተከሳሾቹ በበኩላቸዉ የዐቃቤ ህግ አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ አመልክተዉ ነበር፡፡

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ጥያቄውን መርምሮ ውድቅ አድርጎታል፡፡

ችሎቱ በዛሬው እለት ተሰይሞ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በተገኙበት ጉዳያቸውን ተመልክቷል፡፡

በዚህም ዐቃቤ ሕግ የምስክሮች ዝርዝር ሳይገለጽ ምስክርነታቸው በግልጽ ችሎት እንዲሰማ ሲል ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *