በደማቸዉ ኤች አይ ቪ ኤድስ ያለባቸዉ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች የመከላከያ መድሃኒት መዉሰድ አልጀመሩም፡፡

በኢትዮጵያ ከ 100 ሺህ በላይ ኤች አይ ቪ ኤድስ በደማቸው የሚገኝባቸው ሰዎች እስካሁን ድረስ የኤች አይ ቪ ቫይረስ መከላከያ መድሃኒት መውሰድ አለመጀመራቸዉ ተገልጿል፡፡

የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት እንዳለዉ፤ መድሃኒት ካልጀመሩት በተጨማሪ በኢትዮጵያ በየቀኑ ከ40 ሰዎች በላይ በኤች አይ ቪ ኤድስ ይያዛሉ ብሏል፡፡

በተጨማሪም በሀገራችን በየቀኑ ከ30 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱና ተያያዥ በሽታዎች ህይወታቸውን እንደሚያጡ አማላክቷል፡፡

ፅ/ቤቱ የኤች አይ ቪ ኤድስ ሀጋራዊ የስርጭት ምጣኔውን በተመለከተ እንዳስታወቀው፤ በሴተኛ አዳሪዎች 23 ከመቶ ሲሆን በህግ ታራሚዎች ደግሞ 4 ነጥብ 2 ከመቶ ነው ብሏል፡፡

በመርፌና በስለታማ መሳሪያዎች በኩል ያለው የስርጭት ምጣኔ ደግሞ 39 ከመቶ ሲሆን እንዲሁም በድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ላይ 4 ነጥብ 9 በመቶ መሆኑን ጽ/ቤቱ አስታዉቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *