የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በቻይና ደቡባዊ ክፍል ሩሊ በምትባል ከተማ ከቁጥጥር ውጭ መሆኑ ነዉ የተገለጸዉ፡፡
ይህ የተገለጸዉ የተባለው አዳዲስ የተጠቂዎች ቁጥር በድንገት በሚደረግ ምርመራ መገኘት ከጀመረ በኋላ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ስድስት የሀገሪቱ አካባቢዎች መካከለኛ ስጋት እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡
የሀገሪቷ ጤና ኮሚሽን እንዳስታወቀው፣ በዩናን ግዛት ደግሞ አዳዲስ ተጠቂዎችን እና አምስት አዲስ የበሽታ ምልክቶች መከሰታቸው ሪፖርት መደረጉን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም
