አቶ ደመቀ መኮንን ከጆ ባይደን የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ከሆኑት ጃክ ሱሊቫን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በስልክ ባደረጉት በዚህ ዉይይት አቶ ደመቀ በትግራይ እየተሻሻለ ስላለው ሁኔታ ለጃክ ሱሊቫን አብራርተዉላቸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ሰሞኑን በተካሄደው በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያም መወያየታቸዉም ታዉቋል፡፡

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይን በተመለከተ በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ ያገኛል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የዉጭ ጉዳይ ሚንስትሩ መናገራቸዉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *