የቅዱስ ዻውሎስ ሆስፒታል ከደም ባንክ ጋር በመተባበር ለ 3 ቀናት ደም ለመሰብሰብ መዘጋጀቱን አስታዉቋል፡፡

ሆስፒታሉ ከደም ባንክ ጋር በመተባበር ከዛሬ መጋቢት 30 /2013 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 2/2013 ዓ.ም ድረስ የደም የማሰባሰብ ስራ እንደሚሰራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጿል፡፡

ሆስፒታሉ እንዳለዉ የትኛዉም የደም አይነት ያለው ሰዉ መጥቶ መለገስ እንደሚችል እና አስፈላጊውም ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል::

ከዛሬ ጀምሮ ከሚሰበሰበው ደምም አብዛኛውን የቅዱስ ዻውሎስ ሆስፒታል እንደሚወስድ ተጠቁሟል።

የሚሰበሰበው ደም በወሊድ ምክንያት የደም መፍሰስ ችግር ለሚያጋጥማቸው እናቶች እንደሚውል እና ህብረተሰቡም ደም በመለገስ የበኩሉን እንዲወጣ ሆስፒታሉ ጥሪዉን አቅርቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *