የቻይናዋ ቤጂንግ በፎርብስ መፅሔት ከየትኛውም የአለማችን ከተሞች የቢሊየነሮች መኖሪያ በመባል ቀዳሚ ሆናለች፡፡

ፎርብስ እንዳለው የቻይናዋ ዋና ከተማ ቤጂንግ ባለፈው አመት እንኳን 33 ቢሊየነሮችን ጨምራለች፡፡

እንዲሁም ካሏት የከተማዋ ነዋሪዎች ውስጥ 100ዎቹ ቢሊየነሮች እንደሆኑ መፅሔቱ ባወጣው ዝርዝር ገልጿል፡፡

በተከታይነት ኒው ዮርክ ከተማ ስትቀመጥ 99 ቢሊየነሮችን አሏት ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ቀደም ኒው ዮርክ ከተማ ለሰባት ተከታታይ አመታት ይህንን ዝርዝር በቀዳሚነት ትመራ ነበር ይላል የቢቢሲ ዘገባው፡፡

ቻይና የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝን በፍጥነት መቁጣጠር መቻሏ ለውጤቷ ቁልፍ እርምጃ እንደሆነ ተነግሮ በየጊዜው እያደጉ ባሉት የቴክኖሎጂ ተቋማትና የአክስዮን ገበያዎች ምክንያት ቀዳሚውን ቦታ ለመያዝ እንዳስቻላት ተነግሯል።

ምንም እንኳ ቤጂንግ ከሁሉም የበለጠ ቢሊየነሮች ቢኖራትም የኒው ዮርክ ከተማ ቢሊየነሮች ድምር የተጣራ ሀብታቸው ከቤጂንግ አቻዎቻቸው በ80 ቢሊየን ዶላር ይልቃል ተብሏል፡፡

ቻይና በአጠቃላይ 698 ቢሊየነሮች ሲኖሯት፣ በ724 ቢሊየነሮች ቀዳሚ ወደ ሆነችው አሜሪካ ቀስ በቀስ እየተጠጋች ትገኛለች።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 493 አዲስ ቢሊየነሮች ወደ ዝርዝሩ ውስጥ የገቡ ሲሆን፤ ይህም በየ17 ሰዓቱ አንድ ቢሊየነር ይመነደጋል ማለት ነው፡፡

ከአሜሪካና ቻይና በመከተል ሦስተኛዋ የቢሊየነሮች አገር የሆነችው ሕንድ ናት፤ 140 ቢሊየነሮች እንዳሏት ተበግሯል።

የአማዞን መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆነው አሜሪካዊው ጄፍ ቤዞስ አሁንም የምድራችን ቀዳሚው ባለጸጋ በመሆን ለአራት ተከታታይ ዓመታት እየመራ ይገኛል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *