ጊዜያዊ የንግድ ፍቃድ አውጥተው ህትመት የሚሰሩ ድርጅቶች ከተማዋ ላይ የተዘበራረቀ ገጽታ እየፈጠሩ ነዉ ተባለ፡፡

በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ተሰቅለው ረጅም ጊዜ የሚቆዩ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች እኛን አይመለከቱም ሲል የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሰሪ ማህበር አስታውቋል።

በተለይም ጊዜያዊ ፍቃድ ወስደው ህትመት የሚሰሩ ድርጅቶች ናቸው ለዚህ የሚጠየቁት ሲሉም የማህበሩ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢሳያስ ነግረዉናል።

ከማህበሩ ውጪ የሚገኙ የህትመት ድርጅቶች ከተለያዩ መንግስታዊም ይሁን የግል ተቋማት ጋር ዉል በመዋዋል ስራውን ይሰራሉ፤የህትመት ውጤቶች ስራው ካለቀ በኋላ በአግባቡ ባለመነሳታቸው በተለይም አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ቆሻሻን ሲፈጥሩ እየተመለከትን ነዉ ሲሉም አክለዋል።

ሌሎች የአለም ሀገራት አንድ ከተማ ውስጥ የሚሰቀል ማስታወቂያ የራሱ ጊዜ አስቀምጠውለት በአግባቡ እንደሚያወርዱትም አንስተዋል።

በእኛ ሀገር ግን ይህ ባለመኖሩ የተዘበራረቀ የከተማ ገጽታ እንድንይዝ አድርጓልም ብለዋል ምክትል ሰብሳቢው።

ይህን ለመቅረፍም ከማህበሩ 3 አባል ድርጅቶች ተመርጠው የከተማዋን የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ቋሚ ዲዛይን እንዲሰሩ ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በመቅደላዊት ደረጀ
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *