በሞዛምቢክ ጉዳይ ጎረቤት ሃገራት የአስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርጉ ነዉ።

በሞዛምቢክ እየደረሰ ያለውን ጥቃት አስመልክቶ በአካባቢው የሚገኙ ጎረቤት ሃገራት የአስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሞዛምቢክ የኢስላሚክ ታጣቂ ቡድኖች መስፋፋትን ተከትሎ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ትገኛለች ነዉ የተባለዉ፡፡

ይሄው የሽብር ቡድን በተለይም ከሶስት አመታት በፊት ጀምሮ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲያደርስ መክረሙ ተነግሯል፡፡

በዚህም በነዳጅ ሃብቷ የበለፀገች ናት የሚባልላትን የካቦ ደልጋዶ ግዛት ከተቆጣጠረ ከ2 ሳምንት በላይ ማስቆጠሩን መረጃዎች አመላክተዋል።

ቡድኑ በ3 አመት በፈፀመው የሽብር ጥቃት ከ750 ሺህ በላይ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ማድረጉም ተገልጿል።

የሽብር ቡድኑ የሚያደርሰውን ጥቃት የተመለከቱ ጎረቤት ሀገራት፣ በአደራዳሪነት ለመግባት ቢጠይቁም ሞዛምቢክ ፈቃደኛ እንዳልነበረች ነው የተገለፀው።

በመሆኑም የሀገሪቱ መንግስት በአካባቢው የጅሃዲስቶችን መስፋፋት ሙሉ በሙሉ መግታት አለመቻሉ ነዉ የተነገረዉ።

አሁን ግን 6 የሚሆኑ የሞዛምቢክ ጎረቤት ሀገራት የሽብር ቡድኑ በሞዛምቢክ እያደረሰ የሚገኘውን ጥቃት ለማስቆም ወታደራዊ እርዳታዎችን በማድረግ ቡድኑ የሚደመሰስበትን መንገድ ለማፈላለግ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ቢቢሲ አፍሪካ

ጅብሪል ሙሀመድ
ሚያዝያ 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *