የሩሲያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከግብጹ አቻቸዉ ሳሜህ ሽኩሪ ጋር በካይሮ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በዚህ ወቅት ሰርጌ ላቭሮቭ እንደገለጹት ኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን በህዳሴዉ ግድብ ላይ ያላቸዉ አለመግባባት መፍትሄ የሚያገኘዉ ሀገራቱ ተቀራርበዉ በመነጋገር መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ሀገራቱ ተወያይተዉ ልዩነታቸዉን እንዲፈቱ ሩሲያ ጽኑ ፍላጎት እንዳላት የገለጹት የዉጭ ጉዳይ ሚንስትሩ፣ ለዚህም ሀገራቸዉ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የአፍሪካ ሀገራት የራሳቸውን ችግሮች በራሳቸው እንዲፈቱ ሩሲያ እንደምታበረታታ ሰርጌ ላቭሮቭ በመግለጫቸዉ ወቅት አንስተዋል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም











