አዲስ አበባን የማስዋብ ስራ በሁሉም የከተማዋ መንገዶችና አካባቢዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዳሉት፣ አዲስ አበባን እንደሰሟ ውብ እና ምቹ ከተማ ለማድረግ የተጀመረዉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ ከካቢኔ አባላት ጋር በመሆን ከማዘጋጃ እስከ መስቀል አደባባይ እየተሰራ ባለው የመንገድ ዳር ማስዋብ ፕሮጀክት ችግኝ ተክለዋል።

በዚህ ወቅት ምክትል ከንቲባዋ እንደተናገሩት፣ ለከተማዋ ውበት እና ለእንቅስቃሴ አመቺ የሆኑ የመንገድ አካፋይና ዳርቻዎችን የማስዋብ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በተለይ ከማዘጋጃ ቤት-የአድዋ 00 ኪሎሜትር ጀምሮ እስከ መስቀል አደባባይ ድረስ እየተሰራ ያለው ፕሮጀክት ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ለእግረኛ ፣ለሳይክል እና ለሌሎች አገልግሎቶች ምቹ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ወ/ሮ አዳነች ገልጸዋል።

ይህ የተጀመረዉ ከተማዋን የማስዋብ መልካም እንቅስቃሴም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸዉን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክረተሪ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *