የህወሃት የጥፋት ቡድን በትግራይ 8 አካባቢዎች ሲያደርግ የነበረው የሽፍታ እንቅሰቃሴ በመከላከያ ሠራዊቱ መደምሰሱን ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ ገለጹ፡፡

የህወሃት የጥፋት ቡድን በትግራይ 8 አካባቢዎች ሲያደርግ የነበረው የሽፍታ እንቅሰቃሴ በመከላከያ ሠራዊቱ መደምሰሱን በኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ዘርፍ ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ ገልጸዋል።

ኢቢሲ እንዳለዉ የሠራዊት ግንባታ ዘርፍ ዋና አስተባባሪው ይህን የገለጹት በወቅታዊ የሰራዊቱ ሁኔታ ላይ በሰጡት መግለጫ ነው።

በምስራቅ ደቡብ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ አካባቢ እና ሌሎች አካባቢዎች እርምጃ የወሰደው ሠራዊቱ አስፈላጊ የጦር ቴክኖሎጂ በመጠቀም የጥፋት ቡድኑን ለመደምሰስ እንደተቻለ ሌ/ጄ ባጫ ገልፀዋል።

ከተደመሰሰው የጥፋት ቡድን አካል ውጭ በርካታ የህወሃት ታጣቂዎች ተስፋ በመቁረጥ እጅ እየሰጡ መሆኑም ተገልጿል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *