ይህ አወዛጋቢ ልዩ ምርጫ በ 149 ድንፅ በሃገሪቱ የታችኛው ምር ቤት
የፀደቀ ሲሆን፣ ህግ ከመሆኑ በፊት ግን በላይኛው ምክር ቤት መፅደቅ አለበት ተብሏል፡፡
ፎርማጆ በታችኛው ምክር ቤት ረቂቅ መቀበላቸውን የገለፁ ሲሆን ከ 2 አመት በኋላ የሶማሊያ ህዝብ የራሱን ፕሬዝዳንት ይመርጣል ብለዋል፡፡
ተቃዋሚዎችና ጥቂት የክልል አመራሮች ይህን ረቂቅ ተቃውመውታል፡፡
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአሁኑ የተቃዋሚ ጥምረት አባል ሀሰን አሊ ክሀይሬ ፤ ሀገሪቷ ቀውስ ውስጥ ነች ያሉ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ እንዲገባ አሳስበዋል፡፡
የፎርማጆ ስልጣን የካቲት 8 ማብቃቱን የሚያስታውሱት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ ስልጣን ማራዘም ህገ ወጥ ነው፣ እኛ አንቀበለውም ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል፡፡
ቢቢሲ
በሔኖክ አስራት
ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም











