የኮቪድ-19 ስርጭትን በተመለከተ ሀገር አቀፍ ጥናት ሊካሄድ ነዉ፡፡

ጥናቱ ለአንድ ወር የሚካሄድ ሲሆን ከሚያዝያ 7/2013 እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

በጥናቱ የጤና ሚንስቴርን ጨምሮ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣የዓለም ጤና ድርጅትና ሌሎችም በዘርፉ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ ተቋማት ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡

በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች እንደሚካሄድ የተገለጸዉ ይህ ጥናት የቫይረሱን የስርጭት አድማስና የተጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎችን በጾታና በእድሜ ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ነዉ ተብሏል፡፡

ይህም ለሚደረገዉ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ከፍተኛ ድጋፍ ያደርጋል ነዉ የተባለዉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የጥናቱ ውጤት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዘው የሚወጡ ሕጎች እና መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ ማድረግ ቢያስፈልግ ይህንን ተግባራዊ ለማሻሻል ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የጥናቱ የቦርድ ተወካይ ዶ/ር አበባው ገበየው፤ ከዚህ ቀደም የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የአጭር ጊዜ የዳሰሳ ጥናት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በረድኤት ገበየሁ
ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *