ሱዳን የኢጋድ ሊቀመንበር በነበረችበት ወቅት ኢትዮጵያ ላይ ለፈፀመችው ወንጀል እንድትጠየቅ ኢትዮጵያ አሳሰበች፡፡

ሱዳን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት ወይም ኢጋድ ሊቀመንበር በሆነችበት ወቅት፣ በኢትዮጵያ ላይ ህገ-ወጥ ተግባር መፈጸሟን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቋል።

የሚኒስትሩ ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፣ የሱዳን ወዳጅ አገራትና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ ለፈፀመችው ህገ-ወጥ ድርጊት ተጠያቂ ማድረግ አለባቸው ብለዋል አምባሳደሩ።

ሱዳን ዓለም አቀፍ ህግን በመጣስ በኢትዮጵያ ዜጎች ላይ የግድያና የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሟ እንዳሳዘናት ኢትዮጵያ ገልፃለች።

በመሆኑም አገራት ሱዳን ላይ ጫና እንዲያሳድሩ በአፅንኦት እንጠይቃለን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ሚያዝያ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *