ቦልሶናሮ በእንድራሴዎች ምክር ቤት ምርመራ ሊደረግባቸዉ ነዉ፡፡

የብራዚል እንድራሴዎች ምክር ቤት ፕሬዝደንቱ በ COVID-19 ላይ ያሳዩትን ቸልተኝነት ሊመረምር መሆኑ ተገልጿ፡፡

የብራዚል እንደራሴዎች ምክር ቤት በፕሬዚዳንት ጃየር ቦልሶናሮ የ COVID-19 ወረርሽኝ አያያዝን በተመለከተ ማጣራት መጀመሩን አስታዉቋል፡፡

በብራዚል የሰባት ቀናት አማካይ ዕለታዊ ሞት ከ 3 ሺህ በላይ ሆኖ ቆይቷል፡፡

እናም አሁን ከአሜሪካ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው የሀገሪቱ የሞት ቁጥር ከ 360 ሺህ በላይ ደርሷል፡፡

ብሔራዊ የጤና ጥበቃ ምክር ቤቶች ማክሰኞ ዕለት 3 ሺህ 808 ሰዎች መሞታቸውን እና 82 ሺህ 186 አዳዲስ ተጠቂዎች ማግኘታቸውን ሪፖርት አድርገዋል፡፡

የቀኝ-ዘመም ፖለቲከኛው እና የቀድሞው የጦር ካፒቴን ቦልሶናሮ ወረርሽኙን ከመጀመሪያው በማቃለል “ትንሽ ጉንፋን” በማለት ሲጠሩት ተሰምቷል፡፡

ከዚህም በላይ ሰዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ እንዳያርጉና ባለስልጣናት የሚጥሉትን የእንቅስቃሴ ገደቦች መቃወማቸውን አሁንም ቀጥለዋል፡፡

አልጀዚራ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *