ካለአገልግሎት ቆመው ከነበሩ 2 ሺህ መኪናዎች እስከ 1 ቢሊዮን ብር ድረስ ገቢ ሊገኝ እንደሚችል ተገለፀ።

የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጅንሲ በፌዴራል በጀት ያላቸው ተቋማት ውስጥ ያለ አገልግሎት የተከማቹ ንብረቶችን ከሚያዚያ 4 እስከ ያዝነው ወር ድረስ የምዝገባ ስራውን ሲያከናውን ቆይቶ የደረሰበትን ውጤት አስታውቋል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃጂ ኢብሳ በመግለጫው እንዳሉት እስካሁን ድረስ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ያለ አገልግሎት ተከማችተው የሚገኙ ንብረቶችን አገልግሎት መስጠት የሚችሉትንና የማይችሉትን የመለየት ስራዎችን በ6 ምድቦች ከፋፍለው አቅርበዋል።

1)መኪናዎች እስከ 2 ሺህ
2 ) ማሽነሪዎች እስከ 200
3 )ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በግምት እስከ 700 ሺህ ኪ/ግራም
4) ኮምፒውተሮች እስከ 2 ሺህ 100
5 )ፕሪንተሮች ማባዣ ማሽኖች እስከ 1 ሺሽ 300
6) ደስክቶፕ ኮምፕዩተሮች እስከ 1 ሺህ 800 ድረስ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ስለሆነም ከተመዘገቡትና ከተለዩት ውስጥ መኪናዎችን ወደ አግልግሎት እንዲመለሱ ወይም ደግሞ እንዲሸጡ በማድግ እስከ 1 ቢሊዮን ብር ድረስ ማግኘት እንደሚቻል ነው ያስታወቁት።

ሃላፊው ለአሁኑ ይህንን ይበሉ እንጂ ካለአገልግሎት ቆመው የሚገኙና በርካታ ጥቅም ሊያስገኙ የሚችሉ ገና ያልተመዘገቡ በየተቋማቱ ተከማችተው ያሉ በርካታ ንብረቶች እንደሚገኙም አስታውቀዋል።

ስለሆነም እያንዳንዱ ተቋም ያከማቹትን እንዲያስመዘግቡና እንዲያሳውቁ ለማድረግ፣ በዚህም አገልግሎት ከማይሰጡ ንብረቶች ገቢን ለማግኘት ሲባል፣ ፖሊሲዎችን በማዘጋጀት ወደፊት ከተቋማቱ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሃመድ
ሚያዝያ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *