ኮቪድ – 19 30 ሚሊዮን አፍሪቃውያንን ወደ ድህነት እያስገባ ነው አለ የአለም የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪቃ አገራት ውስጥ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ወደ ድህነት እንደሚገቡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) አስጠቅቋል ፡፡

ድርጅቱ የአፍሪቃ አገራት የተሻለ ክትባት እንዲያገኙ የበለፀጉ አገራት እንዲረዱ ጥሪ አቅርቧል እንድ ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግባ፡፡

አይ ኤም ኤፍ እንደገመተው አንዳንድ የአፍሪቃ አገራት 60 በመቶውን ህዝባቸውን ክትባት ለመከተብ እንዲቻላችው የጤና ወጪዎቻቸውን በ50 በመቶ ከፍ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል ፡፡

ባለፈው ዓመት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪቃ አገራት ኢኮኖሚያቸው በ 2 በመቶ ገደማ ቀንሷል ፡፡

የእንቅስቅሴ ገድቦች የንግድ ድርጅቶችን ጎድተዋል፣ ከገበያ፣ መሸጫ ባለቤቶች እስከ ቱሪስት መዝናኛዎች ፡፡

የወጣት ቁጥር መኖሩ አህጉሪቱን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የረዳ ይመስላል የሚለው ድርጅቱ ፡፡

ይሁን እንጂ የአፍሪቃ ህዝብ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ በመምጣቱ እጅግ በጣም ብዙ ወጣቶች ሥራ ይፈልጋሉ ተብሏል፡፡

ስለዚህም የእንቅስቅሴ ገድቦች በተቻለ ፍጥነት መነሳት አለባቸው ደግሞም በመላው አህጉር ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖን ለመቀነስ ክትባቱ በፍጥነት መሰጠት አለበት ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ሚያዝያ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *