በሃገሪቱ ሁሉም ሙስሊም ሴት የመንግስት ሰራተኞች 2 ሰዓታትን ቀድመው እንዲወጡ የተደረገው በጊዜያዊነት ሲሆን እሱም የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ነዉ ተብሏል፡፡
በዚህም የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የረመዳን ፆም እንደገባ ሴት ሙስሊም የመንግሥት ሰራተኞች በመሉ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የስራ ቀናት ከመደበኛው የስራ መውጫ 2 ስዓት ቀድመው እንዲወጡ ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ባለስልጣንኑ ፈቃድ የሰጠበት ሌላው ምክንያት ነው ያለው ደግሞ የየቀኑ ፆማቸውን ከመፍታታቸው በፊት በሀገሪቱ ባህል የሆነው የኢፍጣር ስነስርዓት በሚደረገው ዝግጅት ላይ ሴቶች እንዲገኙና በምግብ ዝግጅቱ ላይ ቀድመው እንዲሳተፉ በሚል እንደሆም ተገልጿል።
ነገር ግን ይህንን ፈቃድ የሰሙ አንዳንድ የሀገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች፣ ድርጊቱ የወንዶችና የሴቶችን መብት የሚጥሰውን በባህል የሚያረጋገጥ ነው ሲሉ መናገራቸው ተገልጿል።
የመብት ተከራካሪዎቹ እንደሚሉት ሴቶች ከስራ በጊዜ ወጥተው ወደ ቤት ይሂዱና ምግብ ይስሩ፣ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ በተለመደው ሰዓት ይውጡ ማለት ለሴቶች የቤት ስራ ለወንዶች ደግሞ የቢሮ ስራ ተገቢነት እንዳለዉ የተዛባ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነዉ ብለዋል፡፡
ነገር ግን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ ከመብትና ስራን ለሴትና ለወንድ እየመደቡ መስጠቱ ልክ አይደለም በሚል እንጂ ክርክራቸው ከሃይማኖቱ ጋር እንዳልሆነ ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡
ቢቢሲ አፍሪካ
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሃመድ
ሚያዝያ 08 ቀን 2013 ዓ.ም
