በኮሮና ቫይረስ በአንድ ቀን ብቻ የ 42 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በሃገራችን በትናንትናዉ እለት በ24 ሰዓታት ወስጥ ለ7ሺህ 312 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 792 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸዉ የጤና ሚንስቴር አስታዉቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በትናንትናዉ እለት ብቻ 42 ሰዎች በበሽታው ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ነዉ የጤና ሚኒስቴር የገለጸዉ፡፡

ወደ ጽዕኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ መሆኑን የገለጸዉ ሚንስቴሩ በአሁኑ ወቅት 1 ሺህ 028 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

በትናንትናዉ እለት በኮሮናቫይረስ የ42 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 370 ደርሷል።

አሁንም የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመሆኑ የምናደርገዉን ጥንቃቄም ማጠናከር እንዳለብን ለመጠቆም እንወዳለን፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *