ሱዳን 61 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በቁጥጥር ስር አውያለሁ ማለቷ ከዕውነት የራቀ መሆኑን ኢትዮጵያ አስታወቀች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሱዳን ከሰሞኑ 61 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በቁጥጥር ስር አውያለሁ ማለቷ መሠረተ ቢስ ነው ብሏል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን ሱዳን ምንም አይነት የኢትዮጵያን ወታደር በቁጥጥር ስር አላዋለችም ነው ያሉት።

የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ አሁንም ድረስ አልወጣም ነው ያሉት አምባሳደሩ፡፡
ይሁንጅ በሁለቱ አገራት መካከል ምንም አይነት የጦርነት እንቅስቀሴ የለም ብለዋል።
ሱዳን የድንበሩ ጉዳይ ቀጠናዊ ለማድረግ እየሰራች ነው ብለዋል፡፡

ሱዳን ትንኮሳዋን ብትቀጥልም ኢትዮጵያ ግን አሁንም የድንበር ጉዳዩን በዲፕሎማሲ ለመፍታት እምነት አላት ብለዋል ቃል አቀባዩ።

ከዚህ በተጨማሪም ሱዳንና ግብፅ የህዳሴ ግድቡን የድርድር ሂደት እያደናቀፉ እንደሚገኙና የተባበሩት መንግስታት ድርችት በአገራቱ ላይ ጫና እንዲያሳድር የኢትዮጵያ መንግስት በደብዳቤ መጠየቁንም አምባሳደር ዲና አሰታውቀዋል።

ኢትዮጵያ፤ የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካዊያን መፈታት ይችላል የሚል የፀና አቋም ስላላት የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት እንዲቀጥል እየሰራች መሆኑን አረጋግጠዋል።

ግብፅና ሱዳን የድርድር ሂደቱን ከአፍሪካ ህብረት ለማስወጣት የሚያደርጉ ጥረት በኢትዮጵያ ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለዉም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *