ኢትዮ ቴሌኮም ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚውል ከ122 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህወት ታምሩ ርክክቡን ባደረጉበት ሰአት እንደገለፁት፣ ገንዘቡ የተገኘው፣ ኢትዮ ቴሌኮም ከታላቁ የህዳሴው ግድብ ፕሮጀክት ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ጋር በመተባበር ለግድቡ ግንባታ የሚውል በ8100 አጭር የጽሁፍ መልዕክት አማካኝነት በተለያዩ ጊዚያት ከደንበኞቹ የተረከበው እንደሆነ ገልጸዋል።

ዛሬ ርክክብ የተደረገው የ3ተኛው ዙር የገንዘብ መጠንም 122 ሚሊዮን 467ሺህ 670 ብር መሆኑን አስታውቀዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በዚሁ የአጭር የፅሑፍ መልዕክት አማካኝነት በ3ኛው ዙር ያሰባሰበውን ገንዘብ የታላቁ የህዳሴው ግድብ ግንባታን እያካሄደ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስረክቧል።

ቴሌኮሙ እስከዛሬ ድረስ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ብቻ ከ1ኛ እስከ 3ኛው ዙር ድረስ የዛሬውን ጨምሮ ከ252 ሚሊዮን ብር በላይ የተሰበሰበ መሆኑንም ሃላፊዋ አስታውቀዋል።

በጅብሪል ሙሃመድ
ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *