የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሚተገበሩ ሶስት ፕሮጀክቶች የሚውል የ907 ሚሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ አድርጓል።

200 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ውስጥ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚውል ነው።

500 ሚሊዮን ዶላር በሀገሪቱ ለሚከናወን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነት እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ካፒታል ተሳትፎንና ዘላቂ የፋይናንስ አማራጮችን ለማምጣት የሚያስችል ነው ፤ ከዚህ ውስጥ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚውለው የግሉ ዘርፍ በኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ እና አቅርቦት ተሳትፎ እንዲኖረው ለማስቻል ነው፡፡

207 ሚሊዮን ዶላር ስምምነቱ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ – 19 ወረርሽኝ የሚያስከተለውን ጉዳት ለመቀነስ እና የበሽታው መከላከያ ክትባቶችን ውጤታማ እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንዲዳረስ ለማድረግ የሚውል ነው።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴና የዓለም ባንክ ግሩፕ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ተፈራርመዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *