ቱርክ እንቅስቃሴን ሙሉ በሙሉ ለመገደብ መዘጋጀቷን አስታወቀች፡፡

በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አስደንጋጭ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለዉ የቱርክ መንግስት፣ ስርጭቱን ለመግታት ለጊዜዉ እንቅስቃሴን መገደብ የተሻለዉ አማራጭ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ብሏል፡፡

ይህን ተከትሎ በኢስታንቡል የሚገኙ የግብይት ማዕከላት በሸማቾች ተጨናንቀዋል፡፡

ቀደም ሲል በአዉሮፓ ሃገራት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በእጅጉ በተስፋፋበት ወቅት፣ ቱርክ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ዉጤታማ ስራ ሰርታለች በሚል በዓለም ጤና ድርጅት ስትወደስ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

በአሁኑ ወቅት ግን ከፍተኛ ስርጭት ከሚታይባቸዉ ሀገራት መካከል ሆናለች፡፡

በየእለቱ በአማካይ 60 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ እየተጠቁ ሲሆን፣ 300 የሚሆኑ ደግሞ ህይወታቸዉን እያጡ ነዉ፡፡

በዚህም ሃገሪቱ ሙሉ በሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ልትጥል በዝግጅት ላይ መሆኗን አስታዉቃለች፡፡

ለስርጭቱ መጨመር በየጊዜዉ የሚጣሉ ክልከላዎች በቶሎ መነሳታቸዉና ክትባቱን በፍጥነት ተደራሽ ማድረግ አለመቻል በምክንያትነት ተነስተዋል፡፡

በሃገሪቱ ከ 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሲሆን 39 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

በቱርክ ከ83 ሚሊዮን በላይ ከሞሆነዉ ህዝብ እስካሁን ክትባቱን ያገኘዉ 22 ሚሊዮን መሆኑን ዘገባዉ ጠቅሷል፡፡
ቢቢሲ

በሙሉቀን አሰፋ
ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *