ከመንግስት የጤና ተቋማት የተሰረቁ የሳንባ ነቀርሳና የኤች አይቪ ኤድስ መመርመሪያ ኪቶችም መገኘታቸውን ተነገረ

ባለፈው አንድ ወር ከፌዴራል ፖሊስና ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በመዲናዋ በሕገ-ወጥ የመድኃኒት ዝውውር ላይ በተደረገው ጥናት ብዛት ያላቸው መድኃኒቶችና የሕክምና ግብአቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ተከማችተው መያዛቸውን ጠቁመዋል።

በዚህም ለህጻናትና ለእናቶች የሚሰጡ መድኃኒቶችና ከመንግስት የጤና ተቋማት የተሰረቁ የሳንባ ነቀርሳና የኤች አይቪ ኤድስ መመርመሪያ ኪቶችም መገኘታቸውን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ ተናግረዋል።

በህገ ወጥ መልኩ ተከማችቶ የተገኘው መድሃኒት በአዲስ ከተማ በግለሰብ በመኖሪያ ቤት ውስጥ እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ ደግሞ በአንድ መድኃኒት አከፋፋይ ድርጅት የጥበቃ ቤት ውስጥ መገኘታቸውን ነው ተገለጸው።

መድኃኒቱንና የህክምና ግብአቶቹን አከማችተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *